November 26, 2025
November 16, 2025
Around Megenagna, At the Ministry of Revenue, Head Office Meeting Hall
ለውጭ ኦዲተሮች ማህበር አባላት በሙሉ
በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መመሪያ ቁጥር 1096/2017 መሰረት የባለሞያዎች ተከታታይ ሞያ ማጎልበቻ ስልጠናዎች በቦርዱ የሚሰጡ መሆኑን የሚደነግግ ቢሆንም ለ2018 በጀት ዓመት የሞያ ፍቃድ ዕድሳት ተገቢውን የተከታታይ ስልጠና በሞያ ማህበራቱ በኩል እንዲመቻቹ እና ለፍቃድ እድሳትም የህን ማስረጃ ብቻ የሚቀበል መሆኑን ከቦርዱ ጋር በተደረገ ውይይት ወቅት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዚሁ መሰረት የውጭ ኦዲተሮች ማህበር ለአባላቱ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ላይ ህዳር 17/ 2018 ዓ.ም የአንድ ሙሉ ቀን ስልጠና ከገቢዎች ሚኒስቴር እና አካውንቲንግ ሶሳይቲ ኦፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል፡፡
በመሆኑም በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ ተመዘገባችሁ አባላትና ያልተመዘገባችሁ አባላት በዕለቱ ለመገኘት ፕሮግራማችሁን እንድታስተካክሉ እና ቀድሞ በመመዝገብ መሳተፋችሁን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡
ስልጠናው በአቶ ዋሲሁን አባተ በገንዘብ ሚኒስቴር የህግና የታክስ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ይሰጣል
ስልጠና ቦታ፡- ፌዴራል የገንዘብ ሚኒስቴር የስልጠና አዳራሽ / ስድስት ኪሎ/
ሰዓት፡- ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ
ማሳሰቢያ፡- ለታክስ ህግ ስልጠና የምዝገባ ቀን እስከ ህዳር 10/ 2018 ዓ.ም ብቻ ሆኖ ምዝገባውም ቀድሞ በተላከው የጎግል ፎርም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በዚሁ መሰረትም የመጨረሻ ኮንፈርሜሽን ለተመዘገቡ አባላት በኢሜል የምንልክ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
https://forms.gle/TkiuUqcT4bLQetE78
የሰልጣኞች የስልጠና ወጪ ተሳትፎ ድርሻ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
የውጭ ኦዲተሮች ማህበር
Share This Event